ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የፍርድ ቤት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል "የስማርት ኮርት ሲስተም" ይፋ ተደረገ

9 Mons Ago 644
ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የፍርድ ቤት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል "የስማርት ኮርት ሲስተም" ይፋ ተደረገ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት አማካኝነት የበለጸገ ስማርት ኮርት ሲስተም ወይም ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎትን አስመርቋል፡፡

አገልግሎቱ ሰው ሰራሽ አስተዉሎትን መሰረት ያደረገ ድምጽን ወደ ጽሁፍ እና ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች የሚተረጉም ስርዓት ያቀፈ ነው ተብሏል፡፡ 

አገልግሎቱ ዲጂታል መረጃ ዴስክ መተግበሪያ እንዲሁም መረጃ መጠየቂያ እና መቀበያ ቻት ቦት ስርዓትን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡  

ስርዓቱ ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የፍርድ ቤት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ሲሆን ይህም የተያዘ መዝገብ መከታተል፣ የተያዙ ቀጠሮዎችን ማያት፣ ቅሬታዎችን መቀበል እንዲሁም  መረጃዎችን መለዋወጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ስርዓቱ በጊዜና በርቀት ያልተገደበ የፍርድ ቤት አገልግሎት መስጠት ከማስቻሉም በላይ ግልጸኝነት የሰፈነበት የፍርድ ቤት አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስችል ተጠቅሷል፡፡

በመርሃ ግብሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በፍሬህይወት ረታ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top