የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ እያደገ ያለውን የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚመጥን አገልግሎት እንዲሰጥ እየተሰራ ነው - አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

1 Day Ago 91
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ እያደገ ያለውን የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚመጥን አገልግሎት እንዲሰጥ እየተሰራ ነው - አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ እያደገ ያለውን የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚመጥን አገልግሎት እንዲሰጥ እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው የ100 ቀናት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርኃ ግብር ትግብራ በሁሉም ዘርፎች አበረታች ውጤት እያመጣ መሆኑ በዚሁ ወቅት ተመላክቷል።

የትራንስፖርትና ሊጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በዘርፉ የአገሪቷን የኢኮኖሚ እድገት መሸከም የሚችሉና የሎጀስቲክ አገልግሎቱን የሚያሳልጡ ስራዎች ተከናውነዋል።

በአገሪቱ ተግባራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ሴክተሩ ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን እንዳስቻለውም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ውስጥ ለአርሶ አደሩ በወቅቱ የአፈር ማዳበሪያ ማድረስና ለአምራቹም በቂ የሆነ ግብአት ለማቅረብ የሚያስችሉ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

በሩብ ዓመቱ በሴክተሩ በዋናነት የባሕር፣ የየብስ፣ የአየር ትራንስፖርትን ጨምሮ ደረቅ ወደብን የማልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ወቅት በተለይ የግብርናው ዘርፍ እድገት እያስመዘገበ በመምጣቱ ይህንኑ የሚመጥን የቀዝቃዛ ምርቶች ማከማቻ የመገንባት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

እየተመዘገበ ካለው የአገሪቱ እድገት ጋር የሎጂስቲክስ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳደግ የተለያዩ ተግባራት እየተካሔዱ ናቸው ብለዋል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማዘመን ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመሆን ግልጸኝነትንና ተጠያቁነትን የሚያሰፍኑ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አማራጭ የወደብ አገልግሎት ላይም በትኩረት በመስራት የአገሪቱ ገቢና ወጪ ንግድ ያለምንም መስተጓጎል እንዲጓጓዝ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ለዚህም ከጎረቤት አገራት ጋር የሚያገናኙ የመንገድ መሰረት ልማቶችን ከመገንባት አኳያ ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን ተወጥታለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top