የኒውዮርኩ ሴንትራ ሴንትራል እና የአዲስ አበባው ወዳጅነት ፓርኮች ምን አገናኛቸው?

17 Hrs Ago 57
የኒውዮርኩ ሴንትራ ሴንትራል እና የአዲስ አበባው ወዳጅነት ፓርኮች ምን አገናኛቸው?
በአንድ የታሪክ ክስተት ኑሮውን በአሜርካን ሀገር ያደረገው አዲስ ገሰሰ ብዙ ጊዜ የሚያዘወትረው የመዝናኛ ቦታ የኒውዮርኩ ሴንትራን ሴንትራል ፓርክ ነው።
 
ባሕር ተሻግሮ ለግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል በአሜሪካ የኖረው አዲስ በተለያዩ ሀገራት ለሥራ ሲጓዝ በከተማና ከተሜነት ሕይወት ዙሪያ ያለውን ልምድ ከሀገሩ አንጻር መቃኘትም ይወዳል።
 
አሁን ላይ በአዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እየተሰራ ያለው ስራ፣ ባደጉት ሀገራት ሲያስተውለው እና እሱም በሀገሬ ብሎ ሲመኘው የነበረው እንደሆነ ይናገራል።
 
ከመሃል ፒያሳ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ሆነው፣አሮጌውንና አዲሱን ከተማ በትዝታ ወደኋላ ሲቃኘው ልዩነቱ አዲስ ከተማ የተፈጠረ ያህል መሆኑን ነው የሚናገረው።
 
አዲስ አበባ በየቀኑ እያሳየች ያለውን ለውጥ ፒያሳ እየተመላለስኩ ነው የምመለከተው የሚለው አዲስ፣ከዓድዋ ድል ሙዚየም ጀምሮ እየሰፋ ወደ ክልሎች መሄዱ ደግሞ የሚደነቅ ነው ብሏል።
 
ፒያሳ ዶሮ ማነቂያ ሰፈር ከሙሉ ቤተሰቡ ጋር ለበርካታ ዓመታት መኖሩን የሚናገረው አዲስ ገሰሰ፣ የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣የመጥፎ ሽታው ጠረን ለጤናም ለኑሮም ምቹ እንዳልነበረ ያስታውሳል፡፡
 
አሁን ግን በኮሪደር ልማት አካባቢው እጅግ ተቀይሯል የሚለው አዲስ፣ ይህን በማየቴም በጣም ደስተኛ ነኝ ብሏል።
 
ሴንቴራል ፓርክ የኒውዮርክ ከተማ እምብርት ላይ የሚገኝ፣ብዙኃኑ የማህበረሰብ ክፍል ወደ ስፍራው በማቅናት ሙዚቃ የሚሰማበት፣ ሳይክል የሚያሽከረክርበት፣ የመዝናኛ ቦታ በመሆኑ ህጻናትን ይዞ ለመጫወት፣ ከቤተሰብ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ተመራጭ ቦታ ነው ይላል አዲስ።
 
ልክ እንደዚሁ ሁሉ በአዲስ አበባም የወዳጅነት ፓርክ ጊዜ ማሳለፊያ በመሆኑ በአካባቢው የተሰራው ልማት ሳቢና ማራኪ ሆኖ ማህበረሰባዊ መስተጋብር ይፈጥራል ብሏል።
 
ይህ በግልም በጋራም ሆኖ ዘና ለማለት አመቺ ስፍራ ሆኗል የሚለው አዲስ፣ "ወዳጅነት ፓርክን ስጎበኝ ሴንትራል ፓርክን ያስታውሰኛል" ብሏል፡፡
 
ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልስው የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አዲስ ገሰሰ ከኢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
 
በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ እጅግ ታዋቂ ሰው ነው። ለ25 ዓመታት የቦብ ማርሌይ ልጆች ማኔጀር በመሆን ሰርቷል።
 
ታዋቂዋ እጅጋየሁ ሽባባው የመጀመሪያ አልበሟን እንድታወጣ ማኔጀር ከመሆን ጀምሮም ብዙ አበርክቷል። እንዲሁም የቴዲ አፍሮ የቀድሞ ማኔጀርም በመሆን ሰርቷል።
 
የጃኖ ባንድ መስራቹ አርቲስት አዲስ ገሰሰ ኑሮውን ለ40 ዓመታት በባሕር ማዶ አድርጎ የቆየ ቢሆንም አሁን ወደሀገር ቤት ተመልሷል።
 
በመሀመድ ፊጣሞ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top