ኢትዮ ቴሌኮም 5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ በባሕር ዳር ከተማ አስጀመረ

1 Day Ago 59
ኢትዮ ቴሌኮም 5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ በባሕር ዳር ከተማ አስጀመረ
ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛውን ትውልድ (5ጂ) ኔትወርክ አገልግሎት በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ባህርዳር ከተማ አስጀምሯል፡፡
በዚህ መሠረት ኩባንያው በባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ የድርጅት እና ግለሰብ ደንበኞች የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ቴክኖሎጂ ትሩፋት ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
5ኛው ትውልድ የሞባይል አገልግሎት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂግጂጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር ከተሞች እና አካባቢያቸው ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል፡፡
በራሄል ፍሬው

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top