ነጋድራስ የኢቲቪ የስራ ፈጠራ ውድድር መመዝገቢያ

የምዝገባ ቅፅ መመሪያ

ለመመዝገብ ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡ በቡድን መወዳደር ለሚፈልግ አንድ ተወካይ በመምረጥ በተወካዩ በኩል መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ በቁጥር የሚፈለጉ መረጃዎች በቁጥር ብቻ መሞላት አለባቸው፡፡ የገንዘብ መጠኖች ሁሉም በብር የተጠየቁ ናቸው፡፡ ይህ ምዝገባ ለአንድ ምዕራፍ ወይም ለሶስት ወራት የውድድር ጊዜ የሚያገለግል ነው፡፡

ይህ የሥራ ፈጠራ ውድድር በኢቲቪ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሲሆን በሶስት ወራት ውስጥ የተለያዩ የቀረፃ ኘሮግራሞች ይኖሩታል። ኘሮግራሙ በየሳምንቱ በቴሌቪዠንና በሶሻል ሚዲያ ይተላለፋል። የውድድሩ መስፈርቶች የቢዝነሱ ፈጠራ፣ ችግር ፈቺነት፣ አዋጭነት፣ የአተገባበር አመቺነት፣ የካፒታል ተመጣጣኝነት እና የገበያ ተፈላጊነት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በዚህ ውድድር ላይ የስራ ፈጠራ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ሊሳተፍ ይችላል፡፡ ወጣቶች ይበረታታሉ፡፡ በውድድሩ ለመመዝገብ የሚያስፈልገው የውድድሩን ቅፅ ኦን ላይን መሙላት ነው። በውድድሩ ለመሳተፍ ቀጣዩን የመወዳደሪያ ቅፅ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች ማሟላት ያስፈልጋል፡፡

ማስጠንቀቅያ:-
እባካችሁ የመወዳደሪያ ሀሳባችሁን ስትጽፉ ከ 500 ቃላት አይብለጥ

https://negadras.ebc.et/
ግብረመልስ
Top