ቻይና ሲ.አር 450 የሚል ስያሜ የተሰጠውን የዓለማችን ፈጣን ባቡር ይፋ አደርጋለች።
በሀገረ ቻይና የተሰራው ሲ.አር 450 የተሰኘው አዲሱ የቻይና ፈጣን ባቡር ሞዴል በሰዓት 400 ኪሎ ሜትር ይጓዛል ተብሏል።
በተጨማሪም የፈጠራ ቁሳቁሶችን እና ንድፎችን በመጠቀም የባቡሩን አጠቃላይ ክብደት በ10 በመቶ መቀነሰ የተቻለ ሲሆን ይህም ባቡሩን ለማንቀሳቀስ የሚፈለገውን የሃይል መጠን ከመቀነሱም በላይ በአካባቢው ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ይቀንሳል ነው የተባለው።
በሌላ በኩል CR450 የተሰኘው ይህ ፈጣን ባቡር የተሳፋሪዎችን ምቾት እና ደህንነት ለማሻሻል ያስቻሉ የላቀ ቴክኖሎጂዎችን ማሟላቱ ተገልጿል።
ከእነዚህም መካከል የተሻሻሉ ብሬኪንግ ሲስተሞች፣ የቅንጦት እና የቢዝነስ ክላስ ቦታዎችን እና የመመገቢያ ስፍራዎች፣ ይካተቱበታል።
CR450 በቻይና የባቡር ቴክኖሎጅ ፈጠራ ውስጥ ሌላ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን ከሰባት ዓመታት የፈጠራ፣ የምርምር እና የሙከራ ሂደቶች በኋላ ባቡሩ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።