ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ነው

4 Days Ago 280
ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ነው

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና የአመራር አቅምን በሚገነቡ ወቅታዊ ጉዳየች ዙሪያ ስልጠና ጀመሩ።

ስልጠናውን የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስጀምረዋል።

"የሕልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሃሳብ እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና፤ በሀገሪቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በላቀ ስኬት በመፈፀምና ተሞክሮን በማስፋት፣ ተግዳሮቶችን ወደ እድል በመቀየር የህዝብና የሀገርን ጥቅም ለማረጋገጥ በአመራሩ አቅም የሚያዝባቸው ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

የብልፅግና ፓርቲ ከህዝቡ ጋር በመሆን በፈጸማቸው ተግባራት የተጎናፀፋቸውን አንፀባራቂ ድሎች ይበልጥ በማጎልበት በቀጣይ የሚያከናውናቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ አቋምና ዝግጁነት እንደሚፈጠርበትም ተመላክቷል፡፡

በጠንካራ ፓርቲ ጠንካራ የመንግስት አፈፃፀምን እውን በማድረግ ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል በተጨባጭ ለማሣካት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር ይሆናል መባሉንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡  

ዛሬ የተጀመረውና እስከ መስከረም 15 በሚቆየው የስልጠና መድረክ፣ ከሀገሪቱ ሁሉም ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ ከ2 ሺህ በላይ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተሣታፊ ሆናዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top