ዶናልድ ትራምፕ በነበሩበት አካባቢ የተኩስ እሩምታ እንደተሰማ ተገለፀ

3 Days Ago 131
ዶናልድ ትራምፕ በነበሩበት አካባቢ የተኩስ እሩምታ እንደተሰማ ተገለፀ

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፍሎሪዳ በሚገኘው የትራምፕ አለም አቀፍ የጎልፍ ክለብ ውስጥ ጎልፍ እየተጫወቱ በነበረበት ወቅት በአካባቢው ድንገተኛ የተኩስ እሩምታ እንደተሰማ ተገልጿል፡፡

የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ግንኙነት ኃላፊ ስቴቨን ቼዌነግ፤ ትራምፕ በቅርበት በነበሩበት አካባቢ የተኩስ ድምፅ እንደተሰማ አረጋግጠዋል፡፡

ከክስተቱ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለፁት ኃላፊው፤ አሁን በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ማቅረብ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ የሚስጥራዊ ደህንነት ተቋም (ሰክሬት ሰርቪስ) ጉዳዩን ከምዕራብ ፓልም ቢች ከተማ ፖሊስ ጋር በመሆን እየመረመረ መሆኑን ገልፆ፤ አሁን ላይ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ደህና መሆናቸውን ማስታወቁን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

ከሁለት ወራት ገደማ በፊት በዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ከተደረገ በኋላ ዛሬ ያጋጠመው ክስተት በትራምፕ ላይ ያነጣጠረ ይሁን አይሁን እስካሁን ግልጽ አለመሆኑም ነው የተገለፀው፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ ህዳር ወር ለሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፔንሲልቬንያ የምረጡኝ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበሩበት ወቅት የግድያ ሙከራ እንደተሰነዘረባቸው የሚታወስ ነው፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top