የ2017 ዘመን መለወጫ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ ነው

7 Days Ago 385
የ2017 ዘመን መለወጫ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ ነው

የ2017 ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉን አዲስ ተስፋ እና ምኞት በመሻት ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ ደማቅ ስነ ስርዓቶች ያከብሩታል።

ክረምቱ ተሸኝቶ ጋራ ሸንተረሩ በአረንጓዴ ልምላሜ ደምቆ መጪው አዲስ ዓመት አዲስ ነገር ይዞ እንዲመጣ በርካቶች በዚሁ አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ይለዋወጡበታል።

አዲስ ዓመት ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ በታላቅ ስሜት ከሚያከብሯቸው በዓላት አንዱ ሲሆን፤ ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ጎረቤት ቤት ያፈራውን ማዕድ በአብሮነት እየተቋደሰ በጋራ የሚያከብሩት በዓልም ነው።

ኢትዮጵያዊያን ለራሳቸውም ሆነ ለአገራቸው የ2017 አዲስ ዓመት መልካሙን ሁሉ ይዞ እንዲመጣ እየተመኙ በዓሉን በማክበር መስከረም 1 ብለው ተቀብለውታል።

በበርካታ ኢትዮጵያውን ዘንድ አደይ አበባ የአዲስ ዓመት አብሳሪ የመስከረም ወር መለያ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን፤ የተስፋ፣ የልምላሜና የሰላም ምኞት መገለጫ ተደርጎም ይታሰባል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top