ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

11 Hrs Ago 79
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው “ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት በነበረን የሁለትዮሽ ውይይት ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል” ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ እና የፈረንሳይ መንግሥት በብሔራዊ ቤተመንግስት እና በመካሄድ ላይ ባለው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ሥራዎች ላይ ላደረጉት አስተዋፅዖም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በውይይታችን በተለያዩ ዘርፎች የሚኖሩ ትብብሮችን የፈተሽን ሲሆን የፈረንሳይን ኢንቨስትመንት መጨመርን አስመልክቶ ብሎም በትምህርት እና ባሕል ዘርፎች ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በውይይቱ የሀገራቱን ታሪካዊ ትስስር ይበልጥ የመገንባት አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት መስጠታቸውንም አመላክተዋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top