ኢትዮ ቴሌኮም ለብዙ የአፍሪካ ኦፕሬተሮች አርዓያ መሆን የሚችል ተቋም ነው - የጅቡቲ ቴሌኮምና ሱዳቴል ግሩፕ ኃላፊዎች

11 Hrs Ago 46
ኢትዮ ቴሌኮም ለብዙ የአፍሪካ ኦፕሬተሮች አርዓያ መሆን የሚችል ተቋም ነው - የጅቡቲ ቴሌኮምና ሱዳቴል ግሩፕ ኃላፊዎች

በጅቡቲ ቴሌኮም እና ሱዳቴል ቴሌኮሙኒኬሽን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች የተመራ ልዑክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኢትዮ ቴሌኮም የኤክስፒሪየንስ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የኩባንያውን ረዥም የቴክኖሎጂ ጉዞን ጨምሮ ዘመኑ እስከደረሰበት ስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ማዕድን ልማት፣ ስማርት ቱሪዝም የመሳሰሉት የዲጂታል ሶሉሽኖች ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

ልዑካኑ ኢትዮ ቴሌኮም ለዲጂታል ሶሉሽኖች የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና የገነባውን ግዙፍ የመሰረተ ልማት አቅም በማድነቅ፤ ኢትዮ ቴሌኮም ለብዙ የአፍሪካ ኦፕሬተሮች አርዓያ መሆን እንደሚችል አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አክለውም የልምድ ማዕከሉ ፈጠራን በማጎልበት እና የዲጂታል ሥነ-ምህዳሩን በማሳደግ በአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ጉልህ አሻራውን ለማሳረፍ የሚችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው ከሀገር አቀፍ ባለፈ የአፍሪካን ዲጂታል ሽግግር እውን ለማድረግ በመጫወት ላይ ያለውን ሚና በማድነቅ የኢትዮ ቴሌኮም አመራር ለሁለገብ የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት መረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው ማለታቸውን የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ያመላክታል።

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top