በሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መካሄድ ጀመረ

30 Days Ago 340
በሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መካሄድ ጀመረ

በሶማሌላንድ 4ኛው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በስድስት ክልሎች በተዘጋጁ 2 ሺህ 648 የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምፃቸውን እየሰጡ ነው።

በምርጫው የወቅቱ ገዥ ፓርቲ የሰላም፣ የአንድነትና የእድገት ፓርቲ (ኩልምዬ) በመወከል ፕሬዝዳንት ሙሴ ቤሂ፣ ተፎካካሪ ዋዳኒ ፓርቲን በመወከል አብዱሮህማን መሀመድ እና የሰላምና ዊል ፌር ፓርቲን በመወከል ደግሞ ፈይሰል አሊ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ሆነው ቀርበዋል።

በየአምስት አመቱ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሶማሌላንድን የሚመራ ፕሬዚዳንት ቀጥታ የሚመረጥበት ነው።

ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ጎን ለጎን አብላጫ ድምፅ ያገኘና በቀጣይ አስር ዓመታት ከፓለቲካ ማህበርነት ወደ ፓለቲካ ፓርቲነት የሚያድጉ እንዲሁም ፕሬዚዳንታዊ እጩዎችን የማቅረብ መብት የሚኖራቸው ሶስት ፓርቲዎች የሚመረጡበት ምርጫም እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ በፓርቲዎች ምርጫ 7 የፓለቲካ ማህበራት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በሶማሌላንድ ምርጫ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን ከ13 ሺህ በላይ የምርጫ አስፈፃሚዎች ምርጫውን እያስፈፀሙ ይገኛሉ።

እንዲሁም ከ8 ሀገራት የተውጣጡ ታዛቢዎች ምርጫውን እየታዘቡ ይገኛሉ።

በሰሎሞን አበጋዝ (ከሶማሌላንድ ሀርጌሳ)


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top