የዶናልድ ትራምፕ መመረጥ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ መነቃቃት ፈጥሯል

13 Days Ago 274
የዶናልድ ትራምፕ መመረጥ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ መነቃቃት ፈጥሯል

ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚና የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየታየ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የ2024ቱን የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ትራምፕ ማሸነፋቸው ከታወቀ በኋላ በትላንትናው ዕለት ብቻ የአሜሪካን ዶላር የምንዛሪ ዋጋ ሲጨምር፤ አብዛኛዎቹ የአውሮፓ መገበያያ ገንዘቦች ዋጋ ቀንሶ ታይቷል፡፡

የአሜሪካ የዶላር ዋጋ መጨመሩ የአሜሪካን ምርቶች በዓለም ገበያ ያላቸው ዋጋ ከፍ እንዲል፤ የአሜሪካ ዶላር የዓለም ገበያ መገበያያ እንዲሆንና ሸቀጦች በሌሎች የመገበያያ ገንዘቦች እንዲወደዱ ምክንያት ሊሆን ይቻላል ተብሏል፡፡  

ትራምፕ እንደተመረጡ አሜሪካንን የዓለማችን የክሪፕቶ ግብይት መናሀሪያ አደርጋታለሁ ብለው መናገራቸውን ተከትሎ፤ የቢትኮይን የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት ከመቼውም ጊዜ በላይ እድገት አሳይቷል ነው የተባለው፡፡

ለዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝንታዊ ምርጫ 120 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ያደረጉት ቱጃሩ ኤለን መስክ እና መሰሎቹ የዚህ ቴክኖሎጂ ደጋፊ በመሆናቸው ከወዲሁ ተጣቃሚ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡

አሁን በዓለም ያለው የክርፕቶ ከረንሲ ግብይት እድገት ማሳያቱን ተከትሎ በዶላር ያለው ግብይት እንዲጨምርና የበላይነት እንዲዝ ማድረጉም ተጠቅሷል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ እስከ 60 በመቶ በሌሎች ሀገራት ምርቶች ደግሞ እስከ 10 በመቶ ታክስ እንደሚጣል ማሳወቃቸውን ተከትሎ በአሜሪካ በኢኮኖሚው መስክ ለውጥ መታየት ጀምሯል፡፡

ይህ አዲስ የፖሊሲ እርምጃ በአውሮፓ፣ በቻይና፣ በጃፓን እና በሜክስኮ ስጋት መፍጠሩ እየተገለፀ ይገኛል፡፡

ትራምፕ በአሜሪካ ትላልቅ ኩባንያዎች የሚከፍሉት ታክስ ከ20 ወደ 15 በመቶ ዝቅ እንደሚያደርጉ መገለፃቸውን ተከትሎ በአሜሪካ ባለሀብቶች ዘንድ ጥሩ መነቃቃት መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡

የምርጫው ውጤት የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ከሌሎች የመገበያያ ገንዘቦች አንፃር ጨማሪ እንዲያሳይ፤ የካፒታል ገበያ ግብይት አንዲጨምር፤ የቦንድ ሽያጭ ላይ እና በተለያዩ ሸቀጠሸቀጦች የዋጋ ለውጥ እንዲታይ ምክንያት ሆኗልም ነው የተባለው፡፡

ለአብነትም ከ300 ሚሊዮን እስከ 2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ካፒታል የሚንቀሳቀሱ የኤክስቼንጅ ኩባንያዎች ግብይት ጥሩ መነቃቃት እንደፈጠረ ተጠቅሷል፡፡

የትራምፕ መመረጥ በሩሲያ የስቶክ ኤክስቼንጅ ኩባንያዎች ላይ እድግት ሲየሳይ፤ የመኪና አምራቹ የቴስላ ኩባንያ የድርሻ መጠን፤ የቢትኮን ግብይት እና ትላልቅ የአሜሪካ ባንኮች የንግድ እቀቅስቃሴ በጥሩ መነቃቃት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

በላሉ ኢታላ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top