የመከላከያ ሰራዊትን የጀግንነት ታሪክ በዘመኑ የውጊያ ምህዳር በሆነው ሳይበር ምህዳር መድገም እንደሚገባ ተገለፀ

12 Hrs Ago 57
የመከላከያ ሰራዊትን የጀግንነት ታሪክ በዘመኑ የውጊያ ምህዳር በሆነው ሳይበር ምህዳር መድገም እንደሚገባ ተገለፀ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሳይበር መከላከል አቅም ላይ ለሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን 29 የመከላከያ ሰራዊት አባላት አስመርቋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት ሃሚድ በዚሁ ወቅት፤ የሃገር መከላከያ ሰራዊትን የጀግንነት ታሪክ በዘመኑ የውጊያ ሜዳ በሆነው የሳይበር ምሕዳር ላይም መድገም እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የሀገርን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ትብብር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከተቋማት ጋር ለመስራትና እውቀት ለማካፈል ተቋሙ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሃመድ በበኩላቸው፤ የፅጥታና ደህንነት ተቋማት የሀገርን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማስጠበቅ በትብብር ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የመካላከያ ሚኒስቴር ከሳይበር ጥቃት መከላከል የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑንም ገልፀዋል።

በፍሬህይወት ረታ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top