የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ገመገመ

2 Days Ago 125
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ገመገመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባው የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ በጥልቀት ገምግሟል።

በግምገማው በዋናነት የልማት ተነሺዎች የተስተናገዱበትን አግባብ፤ በመንግስት የሚኖሩ የነበሩ የተነሱበት አግባብ፤ መሰረተ ልማት የተሟሉላቸው መሆኑን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የግል ተነሺዎች ደግሞ የካሳ የ3 አመት የቤት ኪራይ እና ምትክ መሬት መውሰዳቸውን፤ የትራንስፖርት አቅርቦት እና የሞራል ካሳ በህጉ መሰረት የተከፈለ መሆኑን የተተነተነ ሪፖርት በየኮሪደሩ አስተባባሪዎች ቀርቦ መገምገሙ ተጠቅሷል።

በግምገማውም ሁሉም ህጋዊ ውል ወይም ሰነድ ኑሯቸው እንዲሁም በመጠለያ በተገኙበት ተጠልለው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ሁሉ የቤት መስተንግዶ እና የቤት መሰረተ ልማቶች በተሟላላቸው እጅግ የተሻለ፣ ንፁህ፣ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉላቸው ቤቶች የተስተናገድ ሲሆን፤ ለመኖር ምቹ አካባቢ ያገኙ ስለመሆኑ እና አንዳንድ ሳይቶች ላይ የመንገድ ደረጃውን ለማሻሻል ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦ ካቢኔው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

ሌሎች ሳይት ላይ አስፈላጊው መሰረተ ልማት ተጠናቆ ነዋሪዎች የየእለት ኑሯቸውን፤ የማህበራዊ ኑሯቸው ሳይበታተን እንደ እድር እና ማህበር ያሉ ማህበራዊ መስተጋብራቸው እንደተጠበቀ መስተናገዳቸው ተጠቁሟል፡፡

በዚህም አቃቂ፣ ገላን፣ ጉራ፣ ፉሪ ሃና፣ አራብሳ አምስትና ስድስት አያት ሶስት፣ ላፍቶ ሃይሌ ጋርመንት እና ለሚኩራ አጠገብ የተሰሩት ሎኮስት፤ አየርጤና ቂርቆስ ለገሃር አካባቢ ፤አራዳ ሰባ ደረጃ አካባቢ በማሃል ከተማ የተገነቡ ቤቶች ላይም መስተንግዶው እና አፈፃፀሙም ጥሩ መሆኑን ካቢኔው ገምግሟል።

የመሠረተ ልማት ቅንጅት አካላት ከከተማ እስከ ፌደራል ተቋማት የነበራቸው ተሳትፎ በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ካቢኔው በጥንካሬ ማንሳቱ ተመላክቷል።

በተጨማሪም መሬት እና ካሳ ምትክ እስካሁን ድረስ ብቻ ከ4.6 ቢሊየን በላይ መከፈሉን፣ የሁለት አመት የቤት ኪራይ መከፈሉን እንዲሁም የቀሪ ነዴዎችም ቅድመ ዝግጅት ሂደት በጥንካሬ መነሳቱ ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል በኮሙኒኬሽን ሥራዎችን በደንብ ደጋግሞ ለሕዝብ መረጃን ማድረስ ላይ ከዚህ በላይ ማድረስ እና ተደጋጋሚ የሚዲያ ሽፋን ያላቸው የመረጃ ስርጭት ለህብረተሰቡ መድረስ እንዳለበት ካቢኔው አሳስቧል። 

መረጃን  የሚያዛቡ እና ሀገር እንዳትለማ ውዥንብር በሚፈጥሩ የተለያዩ ዝንባሌዎች የሚያሳዩ የመረጃ ምንጮችን እና አካላት ላይ ህጋዊ ርምጃ በመወሰድ እንዳለበት አፅንኦት ሰተጥቷል::

በ2ኛው ዙር ኮሪደር ልማት ስራ 2 ሺህ 879 ሄክታር ስፋት፤ 135 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ 240 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ፣ 237 የእግረኛ መንገድ፣ 32 የህፃናት መጫዎች ቦታዎች፣ 79 የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ 114 የታክሲ እና አውቶቡስ መጫኛ እና ማውረጃ ማካተቱ ተጠቀሷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በኮሪደር ልማቱ 58 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች፣ 368 ሄክታር አረንጋዴ ልማት ሽፋን ያላቸው ቦታዎች፣ የ 111 ኪ.ሜ ሳይክል መንገድ፣ 17 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ 106 የህዝብ መረዳጃ ቤቶች፣ 121 ኪ.ሜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር፣ 182 ኪ.ሜ ድሬኔጅ መውረጃ መስመር፣ 50  የተሸርካሪና እግረኛ መተላለፊያ፣ 75 ኪ .ሜ ሪቴይኒንግ (የድጋፍ ግንብ) ስራዎችን የሚያካትት ነው ተብሏል::

ይህንኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ክትትል ማሳደግ፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ የተተገበሩ የአንደኛ ዙር ኮርድር ልማት ልምዶች ተቀምረው ለ2ኛው ዙር በተሻለ ብቃት መስራት እንደሚያስፈልግ፤ ቅንጅታዊ አሰራርም በተጠናከረ መልኩት አሳድጎ በጥንካሬ አሁን ካለው በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካቢኔው ማሳሰቡን የከንቲባ ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top