በከፍተኛ ሁኔታ ገቢያችንን ማሳደግ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፡ - የፋይናንስ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ

5 Hrs Ago 45
በከፍተኛ ሁኔታ ገቢያችንን ማሳደግ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፡ - የፋይናንስ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ
6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፤ ማክሮ ኢኮኖሚው የተረጋጋ የሚሆነው የመንግስት ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ሲያድግ እንደሆነ ገልጸዋል።
 
አዲስ የፋይናንስ ሥርዓት ነው የያዝነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በከፍተኛ ጉዳይ ገቢያችንን ማሳደግ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው ብለዋል።
ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር ታክስ ለጥቅል አገራዊ ምርት ያለው ምጣኔ ዝቅተኛ ነው፤ ይህንን በቀጣይ አራት ዓመታት በ4 በመቶ ማሳደግ ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።
ዘንድሮ ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ከታክስ አንጻር የተሻለ ገቢ መገኘቱን አቶ አሕመድ ጠቁመዋል።
 
በተጨማሪ አዲስ የልማት ጥያቄ ለመፍታት ብለን ከብሔራዊ ባንክ የምንበደርበት አሰራር አብቅቷል ያሉት ሚኒስትሩ፤ የተለያዩ የፋይናንስ ምንጮችን በመጠቀም የልማት ስራዎች እንደሚከናወኑ አስረድተዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top