ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል - ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር)

10 Hrs Ago 44
ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል - ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር)

ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

"ሚዲያ ለብሔራዊ ትርክትና ሀገር ግንባታ" በሚል መሪ ሀሳብ ለመገናኛ ብዙሃን አመራሮችና ባለሙያዎች ለሶስት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቷል።

በሥልጠናው የትርክት እመርታ ከታሪካዊ ስብራት ወደ ሀገራዊ ምልዐት፤ እመርታ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ብልጽግና እና የፖለቲካ እመርታ ከዴሞክራሲ መብት ወደ ሀገራዊ ኃላፊነት በሚሉ ርዕሶች ላይ የስልጠና ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የፖለቲካ እመርታ ከዴሞክራሲ መብት ወደ ሀገራዊ ኃላፊነት በሚል ርዕስ ሰነድ ያቀረቡት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ መሠረት የሚጥሉ በርካታ የሪፎርም ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ አኳያ ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዘበዋል።

በቀጣይም ስለ ሪፎርሙ መነሻዎች፣ ሂደቶች፣ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ህዝቡ በሚገባ እንዲገነዘብ ማድረግ ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለሪፎርሙ ስኬት የሕዝብ ተሳትፎ እንዲጎለበት አስተማሪ ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸውም እንዲሁ፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን የማጥራት እና የፅንፈኝነት አስተሳሰብን መከላከልና መቅረፍ ላይ መስራት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ሀገራዊ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ ትክክለኛና ሚዛናዊ ዘገባዎች መስራት እንዳላባቸውም ነው ሚኒስትሩ ያስገነዘቡት፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top