በደቡብ ሱዳን የደረሰው የጎርፍ አደጋ 1.4 ሚሊዮን ሰዎችን ለጉዳት መዳረጉ ተገለፀ

1 Mon Ago 316
በደቡብ ሱዳን የደረሰው የጎርፍ አደጋ 1.4 ሚሊዮን ሰዎችን ለጉዳት መዳረጉ ተገለፀ

በደቡብ ሱዳን በደረሰው የጎርፍ አደጋ 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸውን እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችም 379 ሺህ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

ለአየር ንብረት ለውጥ በጣም ተጋላጭ የሆነችው ደቡብ ሱዳን በአስርት አመታት ውስጥ እንደዚህ አይነት አስከፊ አደጋ ገጥሟት እንዳማያውቅ ተጠቁሟል።

አሁን ላይ በደቡብ ሱዳን በተከሰተው ከባድ የጎርፍ አደጋ ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የተጎዱ ሲሆን ከ379 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቤት ንብረታቸውና ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መግለጫ አመላክቶ ይህንን ተከትሎ የወባ በሽታ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋም አስጠንቅቋል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በሃገሪቱ 43 አውራጃዎች እና በአቢዬ ክልል ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጎርፍ ተጎድተዋል ብሏል።

በበርካታ ክልሎች የወባ በሽታ መከሰቱን ተከትሎም የጤና አገልግሎቱ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩንና በጎርፍ በተጠቁ አካባቢዎች ያለውን ሁኔታ እያባባሰ መሆኑንም ቢሮው መግለፁን የዘገበው ቲአርቲ ወርልድ ነው።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top