"አዲስ አበባ ፓሪስን መስላለች" - ዳያስፖራው የቱሪዝም ባለሞያ

24 Days Ago 383
"አዲስ አበባ ፓሪስን መስላለች" - ዳያስፖራው የቱሪዝም ባለሞያ

ላለፉት 55 ዓመታት በካናዳ ነዋሪ የሆኑት የቱሪዝም ባለሞያ ልዑል እስጢፋኖስ መንገሻ አዲስ አበባ ፓሪስን መስላለች ሲሉ ተናገሩ፡፡

የቱሪዝም ባለሞያው ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ባለፉት 6 ወራት ብቻ የሀገሪቱ ግስጋሴ የሚደነቅ መሆኑን አንስተው፤ አዲስ አበባን በፈጣን ለውጥ ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡  

የኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት ለዳያስፖራው ትልቅ ኃላፊነት ነው ያሉት ልዑል እስጢፋኖስ፤ ሀገራችን ለማየት በምንመጣበት ጊዜ ብዙ የውጭ ሀገራት ነዋሪዎችን ይዘን መምጣት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በቀጣይ ጥር ወር ላይ ብዙ እንግዶችን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው እንደሚመጡ እና እንግዶቹ ቱሪስቶች ብቻ ሳይሆኑ ኢንቨስተሮችም መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

"እኛ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ነን" ያሉት ዳያስፖራው፤ ለሀገራችን ማንም እስኪሾመን አንጠብቅም ብለዋል፡፡

"ሀገራችንን እኛ ሳናውቃት ለሌሎች ማሳወቅ አንችልም፤ በመሆኑም በውጭ ሀገራት ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን ሀገራችሁን እወቁ" ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የቱሪስት መስህብ ቢኖርም የለሙ ቦታዎች አለመኖራቸው ለቱሪዝሙ እድገት እክል መፍጠራቸውንና የሚፈለገውን ገቢ ለማምጣት አመቺ እንዳልነበሩ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ሁሉን ያሟሉ በመሆናቸው ለጎብኚዎችም ሆነ ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል ብለዋል፡፡

የቱሪዝም መዳረሻዎቹ የስራ እድል በመፍጠር ጭምር ኢኮኖሚው እንዲቀሳቀስ ማስቻላቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ እድገቱ ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ ማገዙን የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ የገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች የቱሪዝም ዘርፉ ይበልጥ እንዲነቃቃ ማስቻላቸውን ተናግረዋል፡፡  

በሜሮን ንብረት


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top