ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቀቀ

3 Days Ago 183
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቀቀ

ከአዲስ አበባ እና ከሀገራችን ከተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜጎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሩጫው ተሳታፊዎች ደኅንነት ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻውን በሚገባ መወጣቱን ገልጿል፡፡

ሁነቱ በሰላም መጠናቀቁ ለኢትዮጵያ መልካም ገፅታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ያስገነዘበው የፌደራል ፖሊስ፤ በዚህም ለፀጥታ አካላት ትብብር ላደረጉት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እና ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃትና በትጋት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላት የላቀ ምስጋና አቅርቧል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top