በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ በመጋፈጥ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ሊሠራ ይገባል፡- ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

5 Days Ago 139
በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ በመጋፈጥ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ሊሠራ ይገባል፡- ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ የተለያዩ ችግሮችን በጋራ በመጋፈጥ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ።
 
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተወጣጡ ምሁራን እና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር እየተወያየ ነው።
 
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስቀረት በሚያደርገው ጥረት የዩኒቨርስቲ ምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
 
የመድረኩ ዓላማም ዩኒቨርስቲዎች እና ሙሁራን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያላቸውን ሚና እንዲወጡ ያለመ እንደሆነም ተገልጿል።
 
ፕሮፌሰር መስፍን በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ በመጋፈጥ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ሊሠራ እንደሚገባ ገልጸው፤ ለዚህም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ምሁራን የድርሻውን ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል።
 
በመድረኩ ከ51 የመንግስት እና 5 የግል ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ 1 ሺህ 200 ተሳታፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
 
በትዕግስቱ ቡቼ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top