አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

14 Days Ago 363
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች
የአውስትራሊያ ፓርላማ የዓለማችን ጥብቅ ሕግ የተባለውን ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሕግ አፅድቋል፡፡
 
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ሕጉ ወጣቶችን ከማሕበራዊ ሚዲያ ጉዳት ለመጠበቅ የወጣ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
 
መጠቀሚያ ቁሶችን ሰጥቶ ልጆችን በማሕበራዊ ሚዲያ ሱስ በማድረግ እና በመከልከል ግራ ተጋብተን ነበር የሚሉት ወላጆች “ልጆቻችን የልጅነት ጊዜ እንዲኖራቸው እኛም እንድናውቃቸው እንፈልጋለን” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
 
እገዳው ስናፕ ቻት፣ ቲክቶክ፣ፌስቡክ ኢንስታግራም እና “X” ን ወይም የቀድሞውን ትዊተር እንደሚያጠቃልል ተጠቅሷል።
 
ከእገዳው ለጻ የሚሆኑ መተግበሪያዎች የመጫወቻ እና የመልዕክት መለዋወጫ ሲሆኑ ዩቲዩብም ከእገዳ ነጻ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
 
ይህንንም ሕግ የማያከብሩ ኩባንያዎች እስከ 50 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል ተብሏል፡፡
 
ሆኖም ግን አተገባበሩ እና የደህንነት አስተማማኝነቱ ላይ በግልፅ የተጠቀሰ ነገር አለመኖሩ ነው የተገለጸው፡፡
 
ሕጉ በሌሎች ሀገራት መሪዎች የተደነቀ ሲሆን ኖርዌይ እና እንግሊዝም በቅርቡ ይህንን ሕግ ለመተግበር ፍላጎት እንዳላቸው አመላክተዋል፡፡
 
ዲጂታል ግሎባል ኦቨርቪው በ2023 ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በዓለም አቀፍ ደረጃ እድሜያቸው ከ8-16 ዓመት የሆነ 40 በመቶ የሚሆኑ ታዳጊዎች የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ናቸው።
 
በአፎሚያ ክበበው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top