ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን አጀንዳዎች ተረከበ

11 Hrs Ago 51
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን አጀንዳዎች ተረከበ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በ7 ክፍሎችና በ64 ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያዘጋጃቸውን አጀንዳዎች በዛሬው ዕለት ተረክቧል።

አጀንዳዎቹን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ከሌሎች ኮሚሽነሮች ጋር በመሆን በጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ከተመራው የምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ አባላት ልዑክ ተረክበዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ኮሚሽኑ ከምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ በጋራ እየሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በተቋማትና በማህበረሰብ ክፍሎች ተደራጅተው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን በአግባቡ እንደሚጠቀምባቸውም አክለዋል፡፡

ሌሎች ተቋማትና ማህበራትም የተደራጁ አጀንዳዎቻቸውን እንዲያስረክምቡ ነው ዋና ኮሚሽነሩ መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው፤ ፖለቲካ ፓርቲዎች አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግ ሚናቸውን መወጣት ይገባቸዋል ማለታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።

የተደራጁት የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎች ለአካታችና አሳታፊ ሀገራዊ ውይይት የሚያግዙ እንደሚሆኑም አስረድተዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top