በአፍሪካ ለዜጎቻቸው ነዳጅን በዝቅተኛ ዋጋ ከሚያቀርቡ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ቢዝነስ ኢንሳይደር አስነብቧል፡፡
ቢዝነስ ኢንሳይደር ባወጣው የሀገራት ዝርዝር ከኢትዮጰያ ውጭ ያሉት ሀገራት በሙሉ የነዳጅ አምራች ሀገራት መሆናቸው ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ ወደ ሃገር ውስጥ አስገብታ ለዜጓቿ የምታቀርበው የነዳጅ ዋጋ የራሳቸውን ነዳጅ ከሚያመርቱ ሀገራት ጋር እኩል ስለመሆኑም ነው ተገለፀው፡፡
ለዚህም መንግስት የዘረጋው የነዳጅ ድጎማ መርኃ ግብር በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ አነስተኛ እንዲሆን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተጠቅሷል፡፡
መንግስት ከባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር እስከ ተያዘው በጀት ዓመት የጥቅምት ወር ባሉት 4 ወራት ውስጥ የ45 ቢሊየን ብር የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ እስመለዓለም ምሕረቱ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ገልፀዋል፡፡
በአፎምያ ክበበው