የኢትዮጵያ አየር ኃይል ''ጸሐይ 2'' የተሰኘች አውሮፕላን ሰራ

15 Days Ago 389
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ''ጸሐይ 2'' የተሰኘች አውሮፕላን ሰራ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት ''ጸሐይ 2 '' የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ያከናወነው የሪፎርም ስራ ኢትዮጽያን የሚመጥንና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን ለመገንባት ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደግሞ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አየር ኃይሉ 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት ''ጸሐይ 2 '' የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች መሆኗንም አክለዋል።

ይህም አየር ኃይሉ በ2030 በአፍሪካ ስመጥር አየር ኃይል ለመሆን የያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በትክክለኛ ጎዳና ላይ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ ገልጸዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top