የኢቢሲ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ወላይታ ሶዶ ስቱዲዮ በይፋ ተመረቀ

1 Day Ago 99
የኢቢሲ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ወላይታ ሶዶ ስቱዲዮ በይፋ ተመረቀ

የኢቢሲ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ወላይታ ሶዶ ስቱዲዮ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

ስቱዲዮውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች መርቀው ከፍተዋል።

የ"ኢቢሲ ወደ ይዘት" የለውጥ ሥራ አካል የሆነው "ኢቢሲ ወላይታ ሶዶ ስቱዲዮ" ህብረተሰቡን በቅርበት ተደራሽ በማድረግ ድምጹን በተሻለ ሁኔታ እንዲያሰማ እንደሚያስችለው ተገልጿል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top