"ጦርነት መቼም መደገም የለበትም" - በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎች

1 Day Ago 111
"ጦርነት መቼም መደገም የለበትም" - በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎች

በተገኘው ሰላም ደስተኞች እንደሆኑ እና ጦርነት መቼም መደገም እንደሌለበት በትግራይ ክልል ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የገቡ የቀድሞ ተዋጊዎች ተናገሩ።

ችግሮችን በጦርነት ለመፍታት መሞከሩ ያተረፈልን ሞትና ጉዳት ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ጦርነት በርካታ እህትና ወንድሞችን አሳጥቶናል በዚህም የውጊያ አስቀያሚነትን አይተናል ብለዋል።

ረሀብ፣ የጓደኛ ሞት፣ የንብረት ውድመት እና ከዜጎች ስቃይ ያለፈ ትርፍ ከጦርነቱ እንዳልተገኘ እና መቼም መደገም እንደሌለበት ገልፀዋል።

ከጦርነቱ ያተረፍነው ሞት እና ኪሳራ በመሆኑ ችግሮችን በንግግር የመፍታት ባህልን መገንባት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

የተገኘውን ሰላም መጠበቅ እንደሚገም የቀድሞ ተዋጊዎች ጠቁመዋል።

ጦርነቱ ዋጋ አስከፍሎንም ቢሆን አልፏል ከዚህ በኋላ ትኩረታችን ሰላምና ልማት ላይ ይሆናል ሲሉም ነው የተናገሩት።

ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን በመቐለ እና በዕዳጋ ሐሙስ የተሃድሶ ማዕከላት የቀድሞ ተዋጊዎችን በማሰልጠን ወደ ቀደሞ ህይወታቸው እንዲመለሱ እያደረገ ነው።

ሰልጣኞች በተሃድሶ ማዕከላት ቆይታቸው ከውጊያ እና ከጦርነት አስተሳሰብ እንዲወጡ የሚያስችል የስነ ልቦና እና የስነ ዜጋ ትምህርት ይሰጣቸዋል።

ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ ደግሞ የመቋቋሚያ የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው ወደ ማህበረሰቡ ይቀላቀላሉ።

በመጀመሪያ ዙር 75ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ ሲሆን፤ ለዚህም ከ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መያዙን ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በንብረቴ ተሆነ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top