"እኛ አፍሪካውያን ጠንካራ አህጉራዊ አንድነት ፈጥረን ወደ ዘላቂ ሰላም የሚያደርሰንን መንገድ መቀየስ አለብን" - አቶ ብናልፍ አንዱዓለም

18 Days Ago 218
"እኛ አፍሪካውያን ጠንካራ አህጉራዊ አንድነት ፈጥረን ወደ ዘላቂ ሰላም የሚያደርሰንን መንገድ መቀየስ አለብን" - አቶ ብናልፍ አንዱዓለም

 

እኛ አፍሪካውያን ብዝኃነታችንን ተጠቅመን ጠንካራ አህጉራዊ አንድነት ፈጥረን ለችግሮቻችን አፍሪካዊ መፍትሄዎች በማበጀት ወደ ዘላቂ ሰላም የሚያደርሰንን መንገድ መቀየስና መጓዝ ይኖርብናል ሲሉ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ተናገሩ፡፡

"የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሐሳብ  አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ለኮንፈረንስ ተካፋዮች ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት፤ ሰላም በባህሪው በሰው ሰራሽ ድንበር የማይገደብ፤ የሁላችንም መሆኑን ተገንዝበን አፍሪካውያን ለሰላም በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መጓዝ አለብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ ብዝኃነቷን ተጠቅማ ጠንካራ አህጉራዊ አንድነት በመፍጠር ለችግሮቿ አፍሪካዊ መፍትሄዎች ማበጀት እንደሚገባትም ገልፀዋል፡፡

ለዚህም የሚሆኑ ሐሳቦችን አቀናጅቶ ወደ ዘላቂ ሰላም የሚያደርሰውን መንገድ መቀየስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ወደ አህጉራዊ ሰላምና ብልጽግና ለሚወስደው መንገድ በአንድነት መቆም፣ መደማመጥና ከድንበር እና ከርዕዮተ ዓለም በላይ የሆኑ አጋርነቶችን መፍጠር ይገባል ማለታቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡  

ሚኒስትሩ አክለውም በተባበረ ክንድ ለመጪው ትውልድ የብሩህ ተስፋ መንገድ ለመጥረግ ዛሬ ላይ አህጉራዊ አጋርነትን ማጠናከር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top