በአርባ ምንጭ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

11 Hrs Ago 47
በአርባ ምንጭ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር ታላቅ ሩጫ በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ሩጫው በህዝብ ተሳትፎና በክልሉ መንግሥት ድጋፍ እየተገነባ ለሚገኘው የአርባ ምንጭ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም ግንባታ ገቢ ለማሰባሰብ እንዲሁም በከተማው የሚከበረውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በጎዳና ላይ ሩጫው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የክልልና የዞን የሥራ ሃላፊዎች፣ ታዋቂው አትሌት ሙክታር ኢድሪስ፣ የ12ቱም ዞኖች ተወካዮች እንዲሁም ከ10 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

መነሻውንና መድረሻውን ጋሞ አደባባይ ባደረገው የጎዳና ላይ ሩጫ በወንዶች አትሌት መክሊት መኮንን አሸናፊ ሲሆን፤ አትሌት ሙሉቀን ታደለ 2ኛ፣ አትሌት ሳሙዔል አብርሃም 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በሴቶች አትሌት ህሊና ሚልኪያስ 1ኛ በመውጣት ስታሸንፍ አትሌት በፀሎት አረጋ 2ኛ፣ አትሌት ሀገር ምንአለ 3ኛ በመውጣት የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top