ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የታደሰውን የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሕንጻ መርቀው ከፈቱ

10 Hrs Ago 60
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የታደሰውን የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሕንጻ መርቀው ከፈቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የታደሰውን የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሕንጻ መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ተገኝተዋል።

የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሕንጻ እድሳት ከተመድ ጠቅላላ ጉባዔ በተገኘ 57 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ መከናወኑ ተገልጿል።

እድሳቱ ታሪካዊና ባህላዊ የኪነ ሕንፃ ይዘቶችን ጠብቆ የተከናወነ ሲሆን፤ ሕንፃው እንደ ኒው ዮርክ እና ጄኔቫ ቢሮዎች ሁሉ ቋሚ ዓውደ ርዕይና አባል ሀገራት ልዩ ሁነቶችን የሚያዘጋጁበት ስፍራ እንደተዘጋጀለትም ተመላክቷል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top