ካፍ ለአባላቱ የሚሰጠውን ዓመታዊ የገንዘብ ድጎማ መጠን አሳደገ

1 Mon Ago 294
ካፍ ለአባላቱ የሚሰጠውን ዓመታዊ የገንዘብ ድጎማ መጠን አሳደገ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለአባላቱ የሚሰጠውን ዓመታዊ የገንዘብ ድጎማ መጠን አሳድጓል::

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተደረገ በሚገኘው 46ኛው የካፍ መደበኛ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ያሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ በአህጉሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዞን ማህበራት ጋር ስብሰባ አድርገዋል።

በዚህ መድረክ ፕሬዝዳንቱ አመታዊ የዞን ማህበራት ድጎማ በፊት ከነበረበት 450 ሺህ ዶላር የ50 በመቶ ጭማሪ ተደርጎበት ወደ 750 ሺህ ዶላር ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ለአባል ሀገራቱ የሚደረገው አመታዊ የገንዘብ ድጋፍም ከ250 ሺህ ዶላር ወደ 400 ሺህ ዶላር እንደጨመረ አብስረዋል።

አብዛኞቹ የካፍ ዞን ማህበራት ባለፉት ሁለት አመታት የእግር ኳስ እድገታቸውን በ50 በመቶ ማሳደጋቸው ተገልጿል።

ፕሬዚዳንቱ በስብሰባው ወቅት ለአህጉሪቱ እግር ኳስ እድገት መንግስትን እና የግሉን ዘርፍ አጋር አድርጎ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በስብሰባው የተካፈሉት የዞን ማህበራት እና የተነጠል ማህራት ፕሬዝዳንቶች በካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና በካፍ ስራ አስፈፃሚ ስራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ለአባል ሀገራቱ የሚሰጠው ድጋፍ ከፍ ማለቱ አስደሳች መሆኑንም ተናግረዋል።

በመድረኩ የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ቀጣይ የትኩረት ነጥቦች የትኞቹ እንደሆኑም በዝርዝር ተቀምጠዋል።

በሀዋርያው ጴጥሮስ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top