አየር መንገዱ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ማረፍ የሚችልበትን አቅም ለመፍጠር የሚያግዝ የመሳሪያ ተከለ ስራ በዚህ ዓመት እንደሚከናወን ተገለፀ

7 Hrs Ago 32
አየር መንገዱ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ማረፍ የሚችልበትን አቅም ለመፍጠር የሚያግዝ የመሳሪያ ተከለ ስራ በዚህ ዓመት እንደሚከናወን ተገለፀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ማረፍ የሚችልበትን አቅም ለመፍጠር የሚያግዝ የመሳሪያ ተከለ ስራ በዚህ አመት ለማከናወን ማቀዱን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ካታጎሪ ሶስት (lll) ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመጀመር ስራው በቀጥታ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ ሰብሳቢነት በተካሄደው በዚህ ውይይት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ሜትሪዮሎጂ ኢንስቲትዩት እና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የስራ ሃላፊዎቹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝተው የሳለስልጣን መስሪያ ቤቱን የኮሚዩኒኬሽን ናቪጌሽንና ቅኝት መሳሪያዎችን የጎበኙ ሲሆን በቀጣይ ለታሰበው ስራ የሚሆኑ ስፍራዎችን እንዲሁ ተመልክተዋል።

ካታጎሪ ሶስት (lll) ማለት አውሮፕላኖች በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ማረፍ የሚችሉበትን አቅም መፍጠር ማለት ሲሆን፤ በዚህም ለስራው እጅግ ወሳኝ የሆነውንና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ሲከሰት አይሮፕላን ለማሳረፍ የሚያግዙ መሳሪያዎችን የተከላ ስራ በዚህ አመት ለማከናወን ማቀዱን የባለስልጣኑ መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ የደህንነት ስጋት እንዳይፈጠር አውሮፕላኖችን ስለማያሳርፍ ችግሩን ለመቅረፍ በሚያደርገው ጥረት ለተጨማሪ ወጪና የጊዜ ብክነት እንደሚጋለጥ ተጠቅሷል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top