በታዋቂው ጂዳህ አለም አቀፍ የገበያ ማዕከል ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ተገለፀ

3 Days Ago 102
በታዋቂው ጂዳህ አለም አቀፍ የገበያ ማዕከል ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ተገለፀ

በሳዑዲ አረቢያ ጂዳህ ከተማ ከሚገኙት ትላልቅ ገበያዎች አንዱ በሆነው በጂዳህ አለም አቀፍ የገበያ ማዕከል ላይ ከባድ የሆነ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተሰምቷል።

በጂዳህ ከተማ የመዲና መንገድ በተባለው ስፍራ የተከሰተውን ከባድ የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከ20 በላይ የእሳት አደጋ መከላከያ ክፍሎች ጥረት ቢያደርጉም የእሳት አደጋው ከፍተኛ ውድመት ማድረሱም ነው የተገለፀው።

የእሳት አደጋው በትናትናው እለት ከቀኑ 6 ሰአት ላይ መከሰቱ የተገለፀ ሲሆን፤ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ሲያደረጉ የነበሩ ሁለት የእሳት አደጋ ባለሙያዎች በአደጋው ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

እሳቱ ከ12 ሰዓታት በኋላ በቁጥጥር ስር ሊውል ቢችልም በአደጋው ብዙ ሱቆች እና ድንኳኖች ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል፡፡

በአደጋው በገበያ ማዕከሉ ውስጥ የነበሩ ብዛት ያላቸው ሱቆችና ድንኳኖች ቢወድሙም እሳቱ በተከሰተበት ወቅት ግብይት ላይ የነበሩ ሰዎች ባለመኖራቸው በሰዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ማስቻሉ ተጠቅሷል።

40 ዓመታትን ያስቆጠረው የጂዳህ አለም አቀፍ ገበያ በጂዳህ ከሚገኙት ጥንታዊ የገበያ ማዕከሎች ዋነኛው እንደነበር የዘገበው ሳዑዲ ጋዜጣ ነው፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top