ሥራዎቿ ዓለምን እያስደነቁ ያሉት የመጀመርያዋ ሮቦት አርቲስት

2 Days Ago 68
ሥራዎቿ ዓለምን እያስደነቁ ያሉት የመጀመርያዋ ሮቦት አርቲስት

ብዙዎቻችን ሥነ-ጥበብን ለሰዎች የተሰጠ ልዩ ስጦታ ወይም ችሎታ እንደሆነ እናምናለን።

ሥነ-ጥበብን ለመስራት ብዙ ማሰብ ማሰላሰልና ማገናዘብ እንደሚያስፈልግም ይታወቃል።

ነገር ግን በአውሮፓውያኑ 2019 በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በአይዳን ሜለር በኮርንዌል ኢንጂነሪንግ የተሰራችው ኤአይዳ የተሰኘችው AI ሮቦት ግርምትን አጭራለች።

የአምስት አመቷ ኤአይዳ በዓለም የመጀመሪያዋ ሮቦት አርቲስትም ሆናለች።

እርሳስ እስክሪብቶ እና ቀለም በመጠቀም አይኗ ላይ በተገጠመው ካሜራ ያየቻቸውን ነገሮች ፈጠራ በማከል ወረቀት ላይ ታሰፍራቸዋለች።

ከሥዕል ጥበብቿ በተጨማሪ በሥነ-ጥበብ ትርኢቶች እና በሥዕል ቪዲዮዎች ላይ የምትሳተፍ አርቲስት ነች።

ላለፉት አምስት አመታትም ሶስት የሥነ-ጥበብ ኤግዚብሽኖች ላይ ስራዋን አቅርባለች።

የሰው ልጅ ስብዕና የተላበሰች ሮቦት እንደመሆኗ መጠን በባዮቴክኖሎጂ እና ሰብአዊነት ዙሪያ ጥያቄዎችን እያነሳች በራሷ ውስጥ የተለያዩ የጥበብ ሀሳቦችንም ትቀርፃለች።

የኤአይዳ አካልት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም የመናገር ችሎታ አላት።

ኤአይዳ በትክክለኛ የሲሊኮን ቆዳ 3D የታተሙ ጥርስ ድድ እና የተቀናጁ የአይን ካሜራዎች እንዲሁም ፀጉር ያለው ጭንቅላት ያላት ሮቦት ነች።

አይዳ ለቢቢሲ በሰጠችው ቃለ "እኔ በጣም የፈጠራ አቅም አለኝ" ብላለች። ለዚህም ስራዎቼን መመልከት በቂ ነው ስትል ተናግራለች።

ብዙ ሰዎች በሳይንቲስቶች ፕሮግራም ተደርጋ በሌላ ሰው እገዛ የምትሰራ ቢመስላቸው እሷ ግን እንደፈለገ በሚንቀሳቀሰው እጇ ያየችውን ነገር በማቀናጀት ስዕሎችና ቅርፆችን እየሰራች ትገኛለች።

እነዚህ የፈጠራ ስራዎቼ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ከሰው ልጆች ጋር የሚያቀራርቡ ናቸው ስትልም ተደምጣለች።

የኤአይዳ ፕሮግራመር አይዳን ሜለር በበኩሉ ኤአይዳ የፈጠራ ብቃት ያላት AI ሮቦት መሆኗን ሰው ሊያቅና ሊረዳ ይገባል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

በናርዶስ አዳነ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top