ኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናል የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያለውን መስተጋብር ያጠናክራል - አቶ ከበደ ዴሲሳ

2 Days Ago 99
ኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናል የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያለውን መስተጋብር ያጠናክራል - አቶ ከበደ ዴሲሳ

ኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናል የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያለውን መስተጋብር እንደሚያጠናክር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው “ተወዳጅ የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት የሆነው ‘ዳንጋ’ ስንሰማ በነበረበት ቅዳሜ የኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ምርቃት መሆኑ ትውስታችንን የሚያመጣ ታሪካዊ ዕለት ነው” ብለዋል።

የአፋን ኦሮሞ የሬዲዮ ስርጭት የጀመረው ኢቢሲ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ከበደ ዴሲሳ፤ ኮርፖሬሽኑ በቋንቋው የ24 ሰዓት ስርጭት መጀመሩ የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያለውን መስተጋብር እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

ይህም የኢቢሲን የተደራሽነት ወሰን ከማስፋት ባሻገር ለኢትዮጵያም ትልቅ ትርጉም እንዳለው አንስተዋል።

ሚዲያ በለውጡ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል አንዱ እንደሆነ በመጥቀስም ሚዲያዎች የተከፈተላቸውን ምህዳር ተጠቅመው በሀገር ግንባታ ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ኮርፖሬሽኑ “ኢቢሲ ወደ ይዘት” በሚል እያከናወነው ያለው መጠነ ሰፊ የሪፎርም ሥራም በይዘት እና በአቀራረብ ከፍ ያለ ተጽእኖ ለመፍጠር እንደሚያግዘው ጠቁመዋል።

ኢቲቪ በሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ የሚገኙ ህዝቦችን ታሪክ፣ ባህል፣ የተፈጥሮ ጸጋ እና ሌሎች ሐብቶችን ለዓለም ለማሳየት ይበልጠ ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top