ኢቢሲ ሀገር በመገንባት ሂደት ውስጥ የህዝብ ድምጽ ሆኖ ይቀጥላል - አቶ ጌትነት ታደሰ

3 Days Ago 103
ኢቢሲ ሀገር በመገንባት ሂደት ውስጥ የህዝብ ድምጽ ሆኖ ይቀጥላል - አቶ ጌትነት ታደሰ

ኢቢሲ ሀገር በመገንባት ሂደት ውስጥ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢቢሲ የኢትዮጵያ ድምጽ በአፍሪካ ደረጃ ከፍ ብሎ የሚነገርበት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሚዲያ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አንስተዋል።

በዛሬው ዕለት በይፋ የተመረቀው የኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናልም ጠንካራ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ያላት ሀገር ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል። 

ወደ 24 ሰዓት ስርጭት የተሸጋገረው ቻናሉ ኢቢሲ በአፍሪካ ደረጃ ተደማጭ የሆነ ሚዲያ ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያግዝም አበክረዋል።

ኢቢሲ ወደ ይዘት በሚል እያከናወነ ባለው የሪፎርም ሥራ ይበልጥ የህዝብ ድምጽ መሆን የሚያስችሉ አዳዲስ ይዘቶችን እና አቀራረቦችን ለተመልካች እያደረሰ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ኮርፖሬሽኑ ለይዘት ተጨማሪ ምንጭ የሚሆኑ ስቱዲዮዎችን በክልል ከተሞች ገንብቶ እያስመረቀ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top