በሶማሌ ክልል ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ በማስረከብ ተጠናቀቀ

3 Hrs Ago 16
በሶማሌ ክልል ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ በማስረከብ ተጠናቀቀ
በሶማሌ ክልል ከጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ አጀንዳዎችን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማስረከብ ተጠናቀቀ።
 
በጅግጅጋ፣ ጎዴና ዶሎ አዶ ከተሞች የመጀመሪያ ምዕራፍ እንዲሁም በሁለተኛ ምዕራፍ ደግሞ በጅግጅጋ ከተማ ባለድርሻ አካላትና የህብረተሰብ ተወካዮች ሲያካሂዱት በነበረው ምክክር አጀንዳዎቻቸውን ለይተው ለኮሚሽኑ በማስረከብ ተጠናቋል።
 
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እና ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም የክልሉን አጀንዳዎች በይፋ ተረክበዋል፡፡
 
በምክክር መድረኩ ከ2 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ተወካዮች፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የክልሉ መንግስት ተወካዮች እንዲሁም ልዮ ልዮ ማህበራትና ተቋማት ተሳትፈዋል።
 
በሰሎሞን አበጋዝ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top