ፓርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ አስታወቀች

3 Hrs Ago 17
ፓርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ አስታወቀች
ፓርቹጋል በትምህርት እና በሌሎችም ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር የመስራት ፍላጎት እንዳላት የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትር ኑኖ ሳምፓዮ ገለጹ።
 
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከፓርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትር ኑኖ ሳምፓዮ ጋር ሁለቱ ሀገራት በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
 
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎችም በሁለቱ ሀገራት መካከል የአካዳሚክ ትብብሮች በሚጠናከሩበትና አሁን ያለው ግንኙነትን በሚሰፋበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል፡፡
 
የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሙዚየም እያቋቋመ መሆኑን የገለጹት ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ፖርቹጋል በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ የነበራትን ተሳትፎና ታሪክ ልታኖር ይገባል ብለዋል፡፡
 
የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትሩ በበኩላቸው፤ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በሌሎችም መስኮች ያላትን የትብብርና የወዳጅነት ግንኙነት አጠናክሮ የማስቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
 
የሀገራቸው መንግስት በትምህርትና በባህል ዘርፍ ያለውን ወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት በማስፋት፤ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል የማሳደግ ፍላጎት እንዳለውም ኑኖ ሳምፓዮ መናገራቸውን የትምህር ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉዊዛ ፋራጋሶ በበኩላቸው፤ሀገራቸው የፖርቸቹጋል ብሔራዊ ቀንን ምክንያት በማድድግ በያሬድ የመዚቃ ትምህርት ቤት የባህል ትርዒት የማቅረብ ፍላጎት እንዳላት አስታውቀዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top