ቻይናውያን ሳይንቲስቶች እውነተኛ 'የማይታይ ካባ' መፍጠራቸውን ገለጹ

10 Mons Ago 848
ቻይናውያን ሳይንቲስቶች እውነተኛ 'የማይታይ ካባ' መፍጠራቸውን ገለጹ

ሳይንቲስቶቹ በሐሪ ፖተር ፊልም ላይ ያለውን ምናባዊ የማይታይ ካባ ወደ እውነተኛው ዓለም በማምጣት ቴክኖሎጂውን ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ አድርገውታል።

ቹ ጁንሃኦ የፈጠራ ሥራውን በቨርቹዋል (በበይነ-መረብ) በተካሄደ ‘ሱፐር ናይት ኦፍ ሳይንስ’ በተሰኘ መሰናዶ ላይ ይፋ ካደረጉ በኋላ በኦንላይን ለዕይታ በቅቷል።

በዚህ ቪዲዮ ላይ የቀረቡት ሁለት ሰዎች፣ አንድ ሰው በካባው ሲሸፈን አለመታየቱን እና ካባው ሲወልቅ የሚታይ ሰው መኖሩን ያሳያሉ። 

‘የማይታየው ካባ’ ብርሃንን የሚቆጣጠሩ እና የማይታይ ስሜት የሚፈጥሩ ቁሳቁሶችን በመጠቀም እንደተሠራ ተገልጿል።

ይህን ፈጠራ አንዳንዶች ቅዠት ነው ቢሉትም ሌሎች ግን ያዩትን ነገር በቅድሞው ቲውተር ላይ አጋርተውታል።

በማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች ላይም ሐሪ ፖተርን በዚህ የፈጠራ ሐሳብ ጊዜውን የቀደመ በማለት ለቴክኖሎጂውም ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸውን ቴላንጋና ቱደይ ዘግቧል።

“የሰው ቴክኖሎጂ በጣም አስደናቂ ነው፣ ከሳይንስ የተገኙ ነገሮች ወደ እውነተኛው ዓለም በገሀድ እየመጡ ነው፣ እነዚህ ነገሮች ለበጎ ጉዳይ እንዲውሉ ምኞቴ ነው" ሲልም አንድ ሰው ሐሳቡን በማኅበራዊ ገጹ ላይ አጋርቷል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top