ጀርመን በድርቅ ለተጎዱ ሀገራት የሚውል የ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

1 Yr Ago
ጀርመን በድርቅ ለተጎዱ ሀገራት የሚውል የ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገች
የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ እና ሱዳን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን በዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በኩል የተበረከተ ሲሆን ፋኦ ድጋፉን ከጀርመን መንግስት መረከቡን አስታውቋል።
ፋኦ በሪፖርቱ እንደገለፀው፣ በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ የምግብ ዋስትና እጦትን እያስከተለ ሲሆን በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን 22 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
በድርቁ ምክንያት በርካታ የቤት እንስሳት መሞታቸውን እና በርካታ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን አመላክቷል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top