በስፔን በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 95 ማለፉ ተገለፀ

5 Hrs Ago 23
በስፔን በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 95 ማለፉ ተገለፀ

በደቡብ ምስራቅ ስፔን በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በርካታ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እና ከፍተኛ ንብረት መውደሙ ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት በሆነችው ቫሌንሺያ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ በትንሹ የ 95 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ ተጠቅሷል፡፡

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተጎጂዎችን የማፈላለግ እና ነፍስ የማዳን ስራ እያከናወኑ ሲሆን፤ ከ 1 ሺህ በላይ ወታደሮች ጉዳት ወደደረሰባቸው አከባቢዎች ለዚሁ ተግባር ተሰማርተዋል ተብሏል፡፡

የስፔን ማዕከላዊ መንግስትም የነፍስ አድን ስራውን ለማገዝ እንዲቻል የአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ ማቋቋሙ ተጠቁሟል፡፡

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ አደጋው ባደረሰው ጉዳት  ከባድ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልጸው፤ የጎርፍ አደጋው በተከሰተበት አካባቢ ያሉ ሰዎች ጥንቅቃ እንዲያደርጉና የነፍስ አድን ስራውን ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ሃገሪቱ በጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች መታሰቢያ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን ማወጇን የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top