እስራኤል በኢራን ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ነግሷል

4 Hrs Ago 35
እስራኤል በኢራን ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ነግሷል

እስራኤል በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ተገልጿል፡፡

ጥቃቱ በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን እና በአቅራቢያዋ በሚገኙ ወታደራዊ የጦር ሰፈሮች ላይ ለበርካታ ሰአታት የቆየ ፍንዳታ ቢያስከትልም ነገርግን እስካሁን በጥቃቱ የተጎዳ ሰው ስለመኖሩና ስለደረሰው ውድመት የተባለ ነገር የለም።

የእስራኤል ጦር ሌሊቱን የፈጸመው ጥቃት ኢራን በእስራኤል ላይ የተኮሰቻቸውን ሚሳኤሎች የሚያመርቱ ተቋማትን፣ የአየር ጥቃት መከላከያ እና የሚሳዔኤል ማስወንጨፊያ ቦታዎችን ዒላማ ማድረጉን ገልጿል።

ኢራን በወታደራዊ ይዞታዎቿ ላይ ጥቃት እንደተፈጸመባት ያረጋገጠች ሲሆን፤ ጥቃቱ ውስን ጉዳት ቢያደርስም በተሳካ ሁኔታ ማክሸፏን አስታውቃለች።

ኢራን ለፈጸመችባት ጥቃት እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት አላት ያለው የአሜሪካ መንግስት፤ ይሁንና እስራኤል በምትውስደው እርምጃ የኢራንን የኑክሌር ማዕከላትን እና የነዳጅ ማምረቻ ተቋማትን ዒላማ ማድረግ እንደሌለባት ማሳሰቡን ቢቢሲ ዘግቧል።

የተፈፀመው ጥቃት በእስራኤል እና ኢራን መካከል ያለውን ውጥረት የበለጠ ሊያከረው እንደሚችል የተነገረ ሲሆን ቀጣናው ወደ ሰፋ ግጭት ሊገባ ይችላል የሚል ስጋትም ተፈጥሯል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top