ኢትዮጵያና ማሌዥያ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

2 Hrs Ago 20
ኢትዮጵያና ማሌዥያ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያና ማሌዥያ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማሌዢያ ኳላላምፑር ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከማሌዢያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከማሌዥያ አቻቸው አንዋር ኢብራሂም ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያና ማሌዥያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳለቸው አንስተው፤ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ለማጠናከር መሰል ጉብኝትና ምክክር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በጉብኝቱ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ዘመናት ያስቆረ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማደስ መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ማሌዥያ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎችም ቁልፍ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሳቸውን ገልፀዋል፡፡

የማሌዥያ የንግድ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስመንትና የንግድ እድሎችን እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋለሁ ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ መጠቀም ለሚፈልጉ የማሌዥያ የግሉ ዘርፍ ተዋናያን ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግም ነው የገለፁት፡፡

ኢትዮጵያ ከተሞችን በማዘመን፣ በመሰረተ ልማት ግንባታ እና በሌሎችም በበርካታ ዘርፎች ከማሌዥያ መማር እንደምትችልም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሌዥያ መንግስትና ህዝብ ላደረጋቸው አቀባል ምስጋና አቅርበው፤ ኢትዮጵያ ወደፊት ከሜሌዥያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማጠናከር ጥብቅ ትብብር ለማጎልበት ቁርጠኛ ናት ብለዋል፡፡

የሜሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም የአፍሪካ መዲና፣ የረጅም ታሪክና የባህል ብዝሃነት ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን መጥተው እንዲጎበኙም ጥሪ አቅርበውላቸዋል፡፡

በላሉ ኢታላ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top