የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጡ የአፍሪካ አየር መንገድ በሚል ተሸለመ

9 Hrs Ago 43
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጡ የአፍሪካ አየር መንገድ በሚል ተሸለመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “Best Overall in Africa award” ሽልማትን አሸንፏል፡፡

አየር መንገዱ በዚህ የሽልማት አሰጣጥ መርሓ ግብር ላይ በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣ በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣ በምርጥ የበረራ ላይ  የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣ በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት እንዲሁም በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

ይህ በ “Airline Passenger Experience Association” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ አየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top