የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ በ23ኛው የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመካፈል በዛሬው ዕለት ቡሩንዲ ቡጁምቡራ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቡጁምቡራ ከተማ ሲደርሱ በቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫርሴት ንዳይሽሚዬ እና በሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጉባኤው በ19ኛው የኮሜሳ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ምክክር የተደረገባቸውን የቀጣናው የሰላምና የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ ሁነኛ መፍትሔ ለማፈላለግ በሚረዱ አሠራሮች ዙሪያ በመወያየት ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡