በኦሮሚያ ክልል በተወሰኑ ዞኖች ለተከሰተው ድርቅ 850 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

1 Yr Ago 670
በኦሮሚያ ክልል በተወሰኑ ዞኖች ለተከሰተው ድርቅ 850 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደረገ
በኦሮሚያ ክልል በተወሰኑ ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ለተጠቁ ወገኖች ባለፉት ሁለት ሳምንታት 850 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ለተጠቁ ወገኖች ባለፉት ሁለት ሳምንታት በገንዘብ 350 ሚሊየን ብር እንዲሁም በዓይነት 500 ሚሊየን የሚገመት በአጠቃላይ 850 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ።
ይህ የተገለጸው በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ለተጠቁ ወገኖች የተለያዩ የሰብዓዊ ደጋፎችን ላበረከቱ አካለት የእውቅና መርሐ ግብር ላይ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ድጋፉ ያደረጉ ተቋማት እና ባለሐብቶችም ድርቁን በዘላቂነት ለመፍታት ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
በዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡
በመለሰ አምዴ

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top