በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ኡስማን ስሩር እንደገለፁት፥ የዝናብ መቆራረጥና በቂ ስርጭት አለመኖር በክልሉ ድርቅ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፡፡
በደቡብ ክልል 342 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የነበረ ምርት በዝናብ እጥረት ምክንያት ከጥቅም ውጭ መሆኑንም የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክር ቤት በዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡን ጠቁሟል።
ለዚህ ችግር ፈጥኖ መድረስ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ኡስማን፤ በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ አካባቢዎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
እስካሁን ችግሩን ለመቋቋም የደቡብ ክልል መንግስት 105 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የፌደራሉ መንግስትም 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ነው የተገለፀው።
በቀጣይም መንግስት ህዝቡን የማስተባበር ስራ እንደሚሰራ መገለፁን ደሬቴድ ዘግቧል።