የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቡራዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤት ፕሮጀክትን ተረከበ

10 Mons Ago
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቡራዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤት ፕሮጀክትን ተረከበ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቡራዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤት ፕሮጀክትን ከተክለብርሃን አምባየ ሕንጻ ተቋራጭ ድርጅት ተረከበ።

ፕሮጀክቱ እ.ኤ.አ በ2017/18 በ708 ሚሊዮን ብር መነሻ በጀት የተጀመረ ነው።

የግንባታ ሂደቱ በአገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች መጓተት የገጠመው ቢሆንም በተያዘለት በጀትና የጥራት ደረጃ መከናወን የቻለ ስኬታማ ፕሮጀክት እንደሆነ በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።

ሚኒስትር በለጠ ሞላ ተቋራጩ ድርጅቱን፣ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤትን እና በስራው ላይ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ባለ ልዩ ተውህቦ እና ተሰጥኦ ሕጻናትና ወጣት ተማሪዎችን ተቀብሎ ተሰጥኦዋቸውን እንዲያሳድጉ የማሰልጠን ዓላማን አንግቦ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገነባ ነው።

የተሰጥኦ ማበልጸጊያው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መመረቁ ይታወሳል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top