በትግራይ ክልል 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ

1 Yr Ago 1233
በትግራይ ክልል 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ

በትግራይ ክልል ከነገ ጀምሮ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ አስታወቀ። 

በኤጀንሲው የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ፍስሃ እንደገለጹት፥ ተፈታኝ ተማሪዎቹ በመቐለ፣ በአክሱም፣ በአዲግራትና በራያ ዩኒቨርሲቲዎች ለአርባ አምስት ቀናት የማጠናከርያ ትምህርት ተሰጥቷቸዋል። 

ከተፈታኞቹም 6 ሺህ 513 ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስና 3 ሺህ አንድ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መሆናቸውን አስረድተዋል። 

ከመካከላቸውም 3 ሺህ 941 ሴቶች እንደሆኑ ጠቅሰዋል። 

ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያበቃቸውን የመልቀቂያ ፈተና ከነገ ጀምሮ እንደሚወስዱና ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ዳይሬክተሩን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል። 

ተፈታኝ ተማሪዎቹ በ2013 ዓ.ም የ12 ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እያለ በወቅቱ በክልሉ ባጋጠመው የፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top