በ2016 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የመንግስትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር የትሞህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

1 Yr Ago 1189
በ2016 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የመንግስትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር የትሞህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪ መጻህፍትና የመምህራን መምሪያዎችን ለመምህራንና ባለድርሻዎች ለማስተዋወቅ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ/ር) ስርዓተ ትምህርቱ የሚተገበረው ከዓለም አቀፍና ከውጭ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚያስተምሩ ሁሉም የመግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መሆኑን ገልፀዋል።

ስርዓተ ትምህርቱም በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በትግራይ ክልል ደግሞ በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል እንደሚተገበርም ተናግረዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ ከሥራና የተግባር የትምህርት አይነቶች በስተቀር በሁሉም የቀለም ትምህርት ዓይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚተገበር ገልፀው፤ የሥራና የተግባር ትምህርቶችም ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

ስርዓተ ትምህርት እየተሻሻለና እየዳበረ እንደሚሄድ የጠቆሙት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ለስርዓተ ትምህርቱ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም መተግበር መጀመሩ ይታወቃል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top